በኦፐሬሽን ሬስኪዩ ኢትዮጵያ፡ ትምህርት ድህነትን ለማሸነፍና የህፃናትን ብሩህ መጻኢ ለማረጋገጥ ትልቁ መንገድ መሆኑን እንምናለን። በ2016 ዓ.ም. (2024 እ.ኤ.አ) የትምህርት ዘመን በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ያመጡትን 10 አበልፃጊ ተማሪዎቻችንን በማሸለምና እውቅና በመስጠታችን ታላቅ ኩራት ይሰማናል። እነዚህ ትጉህ ተማሪዎች በጥንካሬያቸውና በትጋታቸው ማንኛውንም ተፈታታኝ ሁኔታ በትምህርት ማሸነፍ እንደሚቻል አሳይተዋል።
በሽልማት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኦኣርኢ ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ተ. ለተማሪዎቹ አነቃቂ መልዕክት አስተላልፈዋል፡ "ድህነትን ታሪክ ለማድረግ ሁለት መንገዶች አሉ፡ 1ኛ፣ በጥሩ ሁኔታ መማር፣ እና 2ኛ፣ ጥሩ የሙያ ክህሎት ማዳበር ናቸው። ኦፐሬሽን ሬስኪዩ እነዚህ ሁለት ነገሮች በህይወታችሁ እውን እንዲሆኑ ከጎናችሁ ይቆማል። ጠንካራ ሆናችሁ በትጋት ስታጠኑ አሁን ያሉባችሁ ችግሮች ሁሉ ቀላል ይሆናሉ።"
የትምህርት ስኬትን እውቅና መስጠታችን የግል ስኬታቸውን ከማክበር ባለፈ በሁሉም ህፃናት ዘንድ የትምህርትና የክህሎት ፍላጎትን ያጎለብታል። የነገ ተስፋ የሆኑትን ወላጅ አልባና ተጋላጭ ህፃናት (OVC) ብሩህ መጻኢ እውን ለማድረግና አብረውን ለመስራት ለሁሉም አጋሮቻችን ጥሪአችንን እናቀርባለን።