በኦፐሬሽን ሬስኪዩ ኢትዮጵያ ስፖርት ለህፃናት ሁለንተናዊ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው እንምናለን። በክቡራት አጋሮቻችን እና በፊልድስ ኦፍ ፕሮሚስ (FOP) ድጋፍ ለስፖርት ፕሮግራሞቻችን የሚያስፈልጉ የስፖርት ቁሳቁሶች እና አዳዲስ የትዕይንት አልባሳት በማቅረባችን ታላቅ ደስታ ይሰማናል። ለወጣት ስፖርተኞቻችን ጥራት ያላቸውን ቁሳቁሶች ማቅረብ በደህንነት እንዲጫወቱ፣ ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ እና በኩራት እንዲሳተፉ ያደርጋቸዋል።
በዚህ አስደሳች ፕሮግራም ላይ ቢጫ የኳስ ማሊያ የለበሱ ህፃናት በትጉህ አሰልጣኞቻቸው እና ከአለም አቀፍ ደጋፊዎቻቸው ጋር በመሆን በኩራት ተሰልፈው ነበር። ስፖርት ከአካላዊ እንቅስቃሴ ባለፈ እንደ ስነ-ስርዓት፣ የቡድን መንፈስ፣ ፅናት እና ራስን ማመን ያሉ ዋና ዋና የህይወት ክህሎቶችን ያስጨብጣል ይህም ከስፖርት ሜዳው ባሻገር በዘወትር ህይወታቸውና በትምህርታቸው ላይ ከፍተኛ አዎንታዊ ተፅዕኖ ይፈጥራል። ፍቅርን፣ እንክብካቤን እና መልካም እድልን ለሚሹ ህፃናት የተሻለ መጻኢ ጊዜ ለማመቻቸት ከእኛ ጋር ለቆሙት ለ FOP እና ለሁሉም አጋሮቻችን የላቀ ምስጋና እናቀርባለን። በማዕከላችን እየተከናወኑ ያሉትን አነቃቂ ስራዎች ከእኛ ጋር ሆነው እንዲመለከቱ ጥሪያችንን እናቀርባለን።