በኦፐሬሽን ሬስኪዩ ኢትዮጵያ የሴት ልጆችን እቅድና ህልም የሚያስተናቅፉ እንቅፋቶችን በማስወገድ ሙሉ አቅማቸውን እንዲጠቀሙ የማድረግ ትልቅ ቁርጠኝነት አለን። የጤና እና የክብራቸው መጠበቂያ ፕሮግራማችን አካል በመሆን ዕድሜያቸው ከ12 ዓመት በላይ ለሆኑ ሴት ልጆቻችን የንጽህና መጠበቂያ (ሳኒታሪ ፓድ) ድጋፍ ተደርጎላቸዋል። አስተማማኝ የሆነ የንጽህና መጠበቂያ አቅርቦት ማግኘት የሴት ልጆችን ራስን የማመን ብቃት፣ ጤና እና የትምህርት ቆይታ በቀጥታ የሚወስን መሠረታዊ ፍላጎት ነው።
ይህ መሠረታዊ አቅርቦት ካልኖራቸው በርካታ ሴት ልጆች በየወሩ ከትምህርት ገበታቸው እና ከማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ለመቅረት ይገደዳሉ ይህ ደግሞ በትምህርታቸው ወደኋላ እንዲቀሩና ሙሉ በሙሉ ትምህርታቸውን እንዲያቋርጡ ምክንያት ይሆናል። እነዚህን አስፈላጊ ቁሳቁሶች በማቅረብ፣ ምንም አይነት ሴት ልጅ በወርሃዊ ንጽህና ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ትምህርቷ እንዳይቋረጥ እና ክብሯ እንዳይነካ እናደርጋለን። በሴት ልጆች ላይ መዋዕለ ነዋይ ማፍሰስ ማለት በመላው ማህበረሰብ መጻኢ እድል ላይ መዋዕለ ነዋይ ማፍሰስ ነው፤ እንደዚህ ያሉ ቀላል ግን ከፍተኛ ተፅዕኖ ያላቸው ድጋፎች እንቅፋቶችን በማስወገድ ወደ እኩል ዕድል እና ስኬት የሚወስደውን መንገድ ይጠርጋሉ።