በትግራይ ውስጥ አስደናቂ እና መንፈስን የሚያነቃቃ አንድ ሳምንት ካሳለፍን በኋላ፣ እኔና ቴልማ (Thelma) በሰላም ወደ ቤታችን መመለሳችንን ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው። በቆይታችን በሁሉም አራቱ የኦፐሬሽን ሬስኪዩ ኢትዮጵያ (ORE) ማዕከላት በመቀሌ፣ ዓዲግራት፣ ዓድዋ እና በማይጨው የሚገኙትን ድንቅ የሰራተኞች ቡድን በአካል ተገኝተን ለመጎብኘትና ለማናገር ችለናል። በየቀኑ የሚያደርጉትን የፍቅር አገልግሎት በዓይናችን መመልከታችን ትልቅ ስሜትንና መነቃቃትን ፈጥሮብናል።
ይህ ጉብኝት ይህንን ታላቅ ስራ በየቀኑ በቁርጠኝነት እና በፍቅር ከሚያከናውኑት እውነተኛ ባለ ውለታዎች ጋር ፊት ለፊት አገናኝቶናል። እነዚህ ሰራተኞች ባላቸው ፅኑ ቁርጠኝነት እና ፍቅር የብዙ ውድ ህፃናትን መጻኢ እድል እና የህይወት አቅጣጫ በጎ በሆነ መንገድ እየቀየሩ ይገኛሉ። ከመደበኛ ድጋፍ ባለፈ፣ ለህፃናቱ ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ በመፍጠር በፍቅርና በእንክብካቤ ያድጓቸዋል። ለያንዳንዳቸው ሰራተኞች ስላላቸው ከፍተኛ ተወፋይነት የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን፤ በመላው ትግራይ በሚገኙ ህፃናት ህይወት ላይ የሚያመጡት አዎንታዊ ለውጥ ሁልጊዜም ያበራታናል።