በየካቲት ወር (February) ኦፐሬሽን ሬስኪዩ ኢትዮጵያ ለሁሉም የድርጅታችን ቤተሰቦች ልዩ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል የገንዘብ ማሰባሰብ ጥሪ አቅርቦ ነበር። ዛሬ በመቀሌ ማዕከላችን ለሚገኙ ተመዝጋቢ ቤተሰቦች ያንን የተሰበሰበ ቀጥተኛ የገንዘብ ድጋፍ ማደል በመቻላችን ታላቅ ደስታ ይሰማናል። ይህን አቅም ፈጣሪ ድጋፍ እውን ላደረጉልን ለሁሉም ለጋሾችና አጋሮች የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን። ይህ ድጋፋችሁ እርዳታ ለሚሹ ቤተሰቦች እውነተኛ እፎይታንና ተስፋን ሰጥቷቸዋል።
በክፍፍሉ ወቅት እያንዳንዱ ቤተሰብ እንደ ምግብ፣ የሕክምና ወጪ እና መሠረታዊ የቤት ውስጥ ፍላጎቶችን ለመሸፈን የሚያስችል ቀጥተኛ የገንዘብ ድጋፍ አግኝቷል። በወላጆች እና በአሳዳጊዎች ፊት ላይ ይታይ የነበረው ከፍተኛ ምስጋና እና እፎይታ በቦታው ለነበሩት ሰራተኞቻችን በሙሉ ትልቅ ትህትናን እና ደስታን የፈጠረ ነበር። እንደነዚህ ያሉ ድጋፎች የቤተሰቦችን የኢኮኖሚ ጫና ከመቀነስ ባለፈ፣ ክብራቸውን የሚጠብቁ እና ኦኣርኢ ሁልጊዜም ከጎናቸው መሆኑን የሚያረጋግጡ ናቸው።